የማህበራዊ ሚድያ ተፅዕኖ


"የማህበራዊ ሚድያ ተፅዕኖ"

አባት: " ኧረ ተው ልጄ፤ ፌስቡክ አጠቃቀምህ ልክ ይኑረው!"

ልጅ: " አባየ "ኮሜንትህን" ተቀብያለሁ። ግን ሁሌም "ኦንላይን" መሆኔ ምን ችግር አለው?"

አባት: "ችግር አለው እንጅ! ፌስቡክ ላይ ከማዘውተርህ የተነሳ ባህል ወጋችን ዘነጋሀው እኮ።"

ልጅ: "አትሳሳት አባየ ስለ ባህል ወጋችን ጠንቅቄ አውቃለሁ።"

አባት: " እስኪ እንደው በሞቴ በባህላችን መሰረት በአውዳመት ጊዜ የበግ አተራረድ ስርአታችን ምን እንደሚመስል ከመጀመሪያው ጀምሮ ንገረኝ?"

ልጅ: "መጀመሪያ ገበያ ወጥተህ በግ "ሰርች" ታደርጋለህ።"

አባት: " በግ ትፈልጋለህ ማለትህ ነው? እሽ ከዛስ?"

ልጅ: " ከዛ በጉን ቤት ታመጣና መሬት ላይ "ዳውን ሎድ" ታደርገዋለህ።"

አባት: " መሬት ላይ ትጥለዋለህ ማለትህ ነው? እሽ ከዛስ?"

ልጅ: " ከዛማ አንገቱን "ሾርትከት" ካደረክ በኋላ ቆዳውን "ሪሙቭ" ታደርገዋለህ።"

አባት: "ወቸ ጉድ! ከባረከው በኋላ ቆዳውን ትገፋለህ ማለትህ ነው? ሆሆ! ከዛስ?"

ልጅ: "ከዛ በኋላ ሆዱን "ኦፕን" ታደርግና ሆዱ ውስጥ ያሉ "አፕሊኬሽኖች" ታወጣለህ።"

አባት: ጉድ ነው! እሽ ከዛስ?"

ልጅ: " በመጨረሻ "አፕሊኬሽኖችን" ታወጣና "ፎልደር" ላይ ማስቀመጥ ነው።"

አባት: "ስጋው ሰሃን ላይ ታስቀምጠዋለህ ማለትህ ነው ኪኪኪኪ... ከዛስ?"

ልጅ: " በመጨረሻም "ላይክ" ያደረግነውን የስጋ አይነት ወደ ሆዳችን "መፖሰት" ነው።
.
.
.
.
.
.
.
አባት: " አንድ ነገር ረስተሃል ልጄ..ጎረቤቶቻችን "ሼር" እንዲያደርጉ "ኢንቫይት" ማድረግ አለብን!"

No comments:

Powered by Blogger.